Blue Joomla Templates

Comments

Polls
 

Online People

We have 6 guests online

feedback

Duties & Responsiblities

PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Thursday, 02 April 2015 11:02
There are no translations available.

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማት፣ቤቶችናኮንስትራክሽን ቢሮ ሥልጣንና ተግባር

የክልሉ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በዚህ አዋጅ 6/2008 መሠረት የሚከተሉትዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1.የሀገሪቱ የህንፃ ኮድ፣ የዲዛይንና ኮንስትራክሽን ስራ ደረጃዎች በክልሉ ውስጥ መከበራቸውንያረጋግጣል፤

2.በክልሉ መንግስት በጀት ለሚገነቡ የመንግስት ኮንስትራክሽኖች የሚያስፈልጉ ዲዛይኖችናየኮንስትራክሽን ስራ ውሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤

3.በክልሉ መንግስት በጀት የሚከናወኑ የመንግስት ኮንስትራክሽኖች በተገባላቸው ውል መሰረትየጥራት ደረጃቸውና የጊዜም ሆነ የዋጋ ገደቦቻቸው ተጠብቀው መስራታቸውን ይቆጣጠራል፤

4.በክልሉ ውስጥ የስራ ተቋራጮችንና አማካሪዎች ይመዘግባል፤ የሙያ ብቃት ማረጋገጫይሰጣል፤ የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርቶችን ያዘጋጃል፤ አፈፃፀማቸውን ይመዝናል፤ ደረጃያወጣል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ፈቃዳቸውን ይሰርዛል፤ የግንባታ ነክ አለመግባባቶችበሚከሰቱበት ወቅት የግልግል ስራዎችን ያከናዉናል፤

5.በክልሉ ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አቅም እንዲያድግ ተፈላጊውን ድጋፍያደርጋል፤ የግንባታ ቴክኖሎጅዎች እንዲስፋፉ ያበረታታል፣

6.በከተሞች ውስጥ ለሚካሄደው ኢንቨስትመንትም ሆነ በከተማ ቦታና ኮንስትራክሽን ስራዎችለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል፤ ተፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤

7.ዝርዝር ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣ ደንብ የሚደነገግ ሆኖ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትንከተሞች ዕድገት በየጊዜው እያጠና የደረጃ ሽግግር እንዲያደረግላቸው ለክልሉ መስተዳደር ምክርቤት ሃሳብ ያቀርባል፤ የልማት ማዕከላት እንዲሆኑ ሁለገብና የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፤ የከተማአስፋፈርና የዕድገት አቅጣጫውን ያጠናል፤ ይከታተላል፤

8.በከተሞች ውስጥ የያንዳንዱን ከተማ መሪ ፕላን የጠበቁ የመሰረተ ልማት እውታሮችየሚስፋፉበትን ዘዴ ይቀይሳል፤ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ያድርጋል፤

9.የክልሉ ከተሞች ውብ፤ ፅዱና አረንጓዴ እንዲሁም ለኑሮም ሆነ ለስራ ተስማሚ ተወዳዳሪሆነው እንዲገኙ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል፡፡

10.በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን የከተማ አስተዳደሮች በእቅድና በከተማ ፕላን አዘገጃጀትናአፈፃፀም ረገድ ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ጥያቄ ሲቀርብለትም የገጠር ቀበሌ ማዕከላትንናየከተሞችን ፕላን ያዘጋጃል፤ ስራውን በበላይነት ይመራል፤

11.በክልሉ ውስጥ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ይነድፋል፤ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤

12.የግል ሴክተሩን አቅም በማሳደግ ዘርፉ በከተማ ልማት፤ በሪልስቴት ስራወችና በመሳሰሉትእንቅስቃሴዎች በንቃት የሚሳተፍበትን ስልት ይቀይሳል፤

13.የከተሞችን ልማት ለማፋጠንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚያግዙ የተለያዩ ጥናቶችንያካሂዳል፤ በሌሎች እንዲካሄዱ ያደርጋል፤

14.የክልሉ ከተሞች ሁሉን አቀፍ በሆነ ደረጃ የሚጠቁሙባቸውን ልዩ ልዩ ረቂቅ የህግ ማዕቀፎችያዘጋጃል፤ የዕድገት ደረጃቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

15.ከተሞች ከአጋር አካላት ጋር በጋራ የሚሰሩባቸውን ስልቶች በመቀየስ ያልተማከለ አስተዳደርስርዓት የሚጠናክርበትን ዘዴ ይቀይሳል፤

16.የከተማ መሬት ወጭ ቆጣቢና ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል የተለያዩየአስራር ስርዓቶችን ይዘረጋል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤

17.የከተሞችን ልማት ለማፋጠን አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት እንዲደራጅ ለክልሉ መንግስት ጥያቄያቀርባል፤ ሲፈቀድም ተግባራዋ ያደርጋል፤

18.የኢንቨስትመንት ስራዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የልማት አገልግሎቶች የሚውል መሬት በበቂሁኔታ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ያሰጣጡንም ፍትሀዊነት ይከታተላል፤

19.በክልሉ መንግስትና በከተማ አስተዳደሮች ባለቤትነት ስር የሚገኙ ቤቶችን በሚመለከትአግባብ ላላቸው አካላት ተፈላጊውን ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ ያደርጋል፤

20.የከተማው ነዋሪ ህዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠኑ መኖሪያ ቤቶችን ሰርቶ ይጠቀም ዘንድየሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ያደርጋል፡፡

Last Updated ( Wednesday, 13 April 2016 05:51 )
 
free pokerfree poker

Search

Visitors

Members : 102
Content : 29
Content View Hits : 116882

Important Link

Copyright@BOIUD; 2006 EC ---.
All Rights Reserved.